Follow us:
አል ሙኒር ቁርኣን አካዳሚ ፡
የአል ሙኒር ቁርኣን አካዳሚ ፡ አስተምሯችን በሀራችን ዙሪያ በሚገኙ በብቁ እና በተረጋገጡ የቁርአን አስተማሪዎች ይከናወናል። የቀጥታ (online) ትምህርቶች የበይነመረብ ቴክኖሎጂን በመጠቀም እጅግ ዘመናዊን በሆኑ የማስተማሪያ መንገዶች እንሰጣለን ፡፡ በአካል ማዕከላችን ጋር በመምጣት መማር ለምትችሉ አል ሙኒር ማዕከልን ምርጫዎት ያድርጉ።! በአካል ቀርቦ መማር ለማትችሉ ደግሞ! ከቤትዎ ሆነው በተመቾት ሰአት ቁርአንን ለመማር አል ሙኒር ማዕከልን ምርጫዎት ያድርጉ።!
ቁርኣንን_ማንበብ_የፈለገ_ሰው_ሊከተላቸው_የሚገቡ_ሥርኣቶች ►ኒያን ማስገኘት (ሀሣብን መሰብሰብ) የአላህን ውዴታ መፈለግ ►ውዱእ ማድረግ፡፡ ኢስቲዓዛ እና በስመላህ (አኡዙ ቢላህ ሚን አሸ ሸይጧኒ አር ረጂም እና ቢስሚላህ አርረህማኒ አርረሂም) ►በላጭ ጊዜዎችን መጠቀም፡፡ በቀን ውስጥ ካሉት ከወቅቶች ሁሉ በላጭ የሚባለው አላህ ለባሮቹ የሚገለፅበት የሊለት የመጨረሻው አንድ ሦስተኛ ክፍል ነው፡፡ ►ጥሩ ቦታን መምረጥ፥ በላጩ መስጅድ ውስጥ ነው፡፡ ቤት ውስጥም ሆኖ ልብን ከሚሰርቅ እና ሀሳብን ከሚወስድ የራቀ ፀጥ ያለ ቦታ መልካም ነው፡፡ ►ወደ አላህ መጠጋት፡፡ ጭንቅ ጥብብ እንዳለው ሰው በሙሉ ሀሳብ ወደሱ መመለስና ስኬትን መፈለግ ►ቁርኣን በሚያነቡበት ጊዜ ማስተንተን፤ በሀሣብ ከመዋለልና ከመዳከር መቆጠብ ►አብሣሪ የሆኑ የቁርኣን አንቀፆች ሲያጋጥሙ በስሜት መንጎድና አላህን ከእዝነቱ መጠየቅ፡፡ አስጠንቃቂ የሆኑ አንቀፆች ሲያጋጥሙደግሞ መደንገጥ፤ አላህ ከነርሱ ከተቆጣባቸው እንዳያረገን መለመን፡፡ ►የቁርኣን ንግግሮች እኛን እያንዳንዳችንን በግል እንደሚመለከቱንና አላህም እኛን እያናገረ እንደሆነ አድርገን ማሰብ፡፡ በዚህም ከኛ ምን እንደሚፈለግ ለመገንዘብ ለረጅም ጊዜ ቆም በማለት ስለ ክልከላዎች እና ትእዛዛቱ ማስተንተን
ቁርኣን ለአነበበው ሰው የሚያበረክተው ሽምግልና عن أبي أمامة البَاهِلي رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال : « اقْرَءُوا الْقُرْآنَ فَإِنَّهُ يَأْتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ شَفِيعًا لأَصْحَابِهِ » رواه مسلم . ከአቢ ኡማመተል ባሂሊይ (ረዲየሏሁ ዓንህ) እንደተዘገበው ፣ የአሏህ መልእክተኛ (ሶልለሏሁ ዓለይሂ ወሰልለም) ፡ “ቁርኣንን አንብቡ። እሱ የቂያማ እለት ለአንባቢው ሰው ሸምጋይ ሆኖ ይመጣልና” ብለዋል። ሙስሊም ዘግበውታል
رَبيع الأوّل 15 1443

ቁርኣንን መሐፈዝ ከዱንያ መጣቀሚያ ይበልጣል


عن عقبة بن عامر الجهني قال : خرج علينا رسول الله صلى الله عليه وسلم ونحن في الفة فقال : ( أيكم يحب أن يغدو إلى بطحان والعقيق فيأخذ ناقتين كوماوين زهراوين بغير إثم بالله ولاقطع (قطيعة) رحم ؟ ) قالوا : كلنا يا رسول الله ، قال : (فلئن يغدو أحدكم كل يوم إلى المسجد فيتعلم آيتين من كتاب الله خيرا له من ناقتين وإن ثلاث فثلاث مثل أعدادهن من الإبل). رواه مسلم
ዑቅበቱ ቢን ዓሚር አል ጁሀኒ እንዲህ ብለዋል :- ” እኛ በሱፋ ( መጠጊያና መጠሊያ የሌላቸው ሰሐባዎች የሚኖሩበት በመስጂድ ውስጥ የሚገኝ ቦታ ) ሳለን ረሱል ሠዐወ ወደኛ መጡና እንዲህ አሉ ” የትኛችሁ ነው ወደ በጥሓን እና ዐቂቅ ማልዶ (ሲያበቃ ) በአላህ ላይ ሳያምፅ ዝምድናም ሳይቆርጥ ሁለት ሻኛቸው ትላልቅና የሰቡ ግመሎችን መውሰድ የሚወድ!? “
(እኛም) ” ሁላችንም (እንወዳለን) ” አልናቸው።
” አንዳችሁ በየቀኑ ወደ መስጂድ ቢማልድና ከአላህ መፅሐፍ (ከቁርኣን) ሁለት አንቀፃትን ቢማር ከሁለት ግመሎች ይበልጥለታል። ሶስት ከሆነ ከሶስት (በአንቀፃቶቹ ) የቁርኣን አንቀፅ ቁጥር ልክ ግመሎች! ” ሙስሊም ዘግበውታል

Share This:

Leave Your Comments

Your email address will not be published.

Copyright 2020, Al Munir Qur’anic Academy All Rights Reserved

Translate »
Open chat